በእነ ክርስቲያን ታደለ የክስ መዝገብ ላይ ብይን ለመስጠት ተቀጠረ


ዛሬ በፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት አራተኛኛ ወንጀል ችሎት በእነ አስር አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ ዘጠኝ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ለፍርድ ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ተከሳሾች በዐቃቤ ሕግ የቀረበባቸውን ክስ መሠረት በማድረግ የክስ መቃወሚያቸውን ለፍርድ ቤቱ ያቀረቡ ሲሆን ፍርድ ቤቱም የክሰ መቃወሚያቸውን በመቀበል ዐቃቤ ሕግ

ለቀረበው የክስ መቃወሚያ መልስ እንዲያዘጋጅ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በመጨረሻም ፍርድ ቤቱ የክስ መዝገቡን እና መቃወሚያውን መርምሮ ብይን ለመስጠት ለታኅሳስ ሀያ አንድ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares