Thu. Feb 27th, 2020

Yeahun

Ethiopian News

ህወሃት ”የአናሳ ብሔረሰቦች ኮሚሽን” ለማቋቋም እየሰራ መሆኑ ተሰማ

አገሪቱ በአሐዳዊ እና ጨፍላቂዎች እጅ ወድቃለች የሚል ፕሮፖጋንዳ የሚዘራው ህወሃት የሚይዝ የሚጨብጠውን አጥቷል። የፌደራሊስት ጉባኤ በሚል ተላላኪዎችን ሁለት ዙር መቀሌ ያመላለሰው ህወሃት ባለፈው ሳምንት ካደረገው ጉባዔ በኋላ ማይኖሪቲስ ኮሚሺን በሚል አነስተኛ የሕዝብ ቁጥር ያላቸውን የማንነት ቡድኖች የሚያቅፍ “የብሔረሰቦች ኮሚሽን” ለማቋቋም እየሠራ መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ለ27 አመት ጥያቄያቸውን አፍኖ ከቆየበት አሁን ክልል ሁኑ እያለ በማደራጀት የገንዘብ እና ፕሮፓጋንዳ ድጋፍ እየሰጣቸው ያሉ የደቡብ ብሔረሰቦችን የአናሳዎች ኮሚሽን ላይ ሙሉ ለሙሉ ለማካተት የየብሄረሰቡን ልሂቃን ለመወትወት በዝግጅት ላይ ይገኛል።

ከእያንዳንዳቸው ከአናሳዎቹ የህግ ባለሙያዎችን እንዲያሰባስቡ ይፋዊ ጥሪ ለማቅረብ የሚያስችል የኮሚሽኑን አደረጃጀት በዝርዝር የሚያሳይ ማዕቀፍ በፕሮፖዛል መልኩ በማዘጋጀት ላይ መሆኑ ተሰምቷል።

ኢትዮጵያን ማይኖሪቲስ ኮሚሺን ለማደራጀት የፕሮፖዛል ዝግጅቱን በበላይነት እያስተባበረ ያለው የህወሃት የፖሊት ቢሮ አባል የሆነው አስመላሽ ወልደስላሴ ሲሆን÷

በዝግጅቱ ላይ ተሳታፊ ከሆኑት አካላት ዋና ዋናዎቹ ዶር አሰፋ ፍስሃ ዶር መንበረፀሐይ ታደሠ መረሳ ፀሃየ  ዘርዓይ ወልደሰንበት እና በመቀሌ የኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ የህወሃት አባላትና ደጋፊዎች ይገኙበታል።

ኮሚሽኑ ሊጨፈልቃችሁ ነው ከተባለው የዐቢይ አህመድ መንግስት ጋር የሚደራደር እና ማይኖሪቲ የሚላቸው ብሔረሰቦች ቬቶ ፓወር ድምፅን በድምፅ የመሻር መብት እንዲይዙ የሚያስገድድ አላማ መያዙ ታውቋል።

ባለሙያዎችን ካሰባሰበ በኋላ ጉባኤውን በመቀሌ ለማድረግ አቅዶ የነበረ ቢሆንም መልሶ በሐዋሳ እንዲደረግ መወሰኑ ተሰምቷል። ሐዋሳ የታጨችበት ዋነኛ ዓላማ በደቡብ ክልል ያለውን የመዋቅር ለውጥ ክልልነት ጥያቄ ለማቀጣጠልና ክልሉ ከሃምሳ ስድስት በላይ ብሄረሰቦች የሚኖሩበት በመሆኑ ነው።

በቀጣይ የታሰበውን የሐዋሳውን መድረክ ኢትዮጵያን ማይኖሪቲስ ኮሚሺን ለማመቻቸት የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈጉባዔ እና የህወሃት የፖሊት ቢሮ አባል የሆነችው ወሮ ኪሪያ ኢብራሂም የቤት ስራ ተሰጥቷታል ። ሴትዮዋ የምትመራውን የፌዴራል ተቋም ለዚሁ ዓላማ እንደምትጠቀምበት መረጃው ያመለክታል።

ለ27 አመት በሞግዚት የእጅ አዙር አስተዳደር የመራቸውን ክልሎች አማራ እና ኦሮሞ ማይኖሪቲስ ብሔሮችን አጥፊ ጨፍላቂ እና ተገንጣይ ብሎ በመመደብ ከፍተኛው የኢትዮጵያ መንግስት ስልጣን በኦሮሞ እና አማራ እጅ እንዳይገባ ሲሠራ ኖሯል።

የሚታዘዙትን መሪዎች ከደቡብ በማፈራርቅ በለመደው ሞግዚትነት ሊመራ አቅዶ የነበረው ህወሃት ጭራቅ አድርጎ በሳላቸው የአማራ እና ኦሮሞ አመራሮች ትብብር ተወግዷል። ከዚያ ወዲህ አሃዳዊነት መጣ ፌደራሊስት ተሰብሰብ ሲል ከርሞ አሁን የኮሚሽን እቅድ አምጥቷል።

አናሳ ብሔሮች ልዩ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸው እያለ ሲሾምላቸው ሲሽርላቸው የነበሩት ክልሎች ደግሞ ዛሬ ከህወሃት ወታደራዊና ፖለቲካዊ ጫና ወጥተን በኢህአዴግ መዋሃድ ከባይታወርነት ወጣን እያሉ ይገኛሉ።

ለ27 አመታት ወደከፍተኛ የአገር ስልጣን እንዳይመጡ የገፋቸው የኦሮሞ እና አማራ አመራሮች አራት ኪሎ መግባት እንቅልፍ ቢነሳው የሌሎች ብሔረሰቦች ጠላት አድርጎ ለመሳል የገንዘብ የፕሮፖጋንዳ የስትራቴጂ እና የሕገ-ወጥ ተቋም ምስረታ ወኪል በመሆን የግጭት ምንጭ ሆኗል። ትናንት ዋጋ ከፍዬ ነፃ እንዳወጣሗችሁ ዛሬም አደጋ መጥቶባችሗል አድናችሗለሁ በሚል ኀይል በማሰባሰብ ላይ ይገኛል።

27 አመት የኖረባቸው ህገመንግስት የፌደራል አሠራር በየደረጃው ያሉ ምክርቤቶችን ሁሉ የብሔሮች ዋስትና ናቸው ሲል እንዳልነበር ዛሬ በኮሚሽን ዋስትና ላስጠብቅ ማለቱ አነጋጋሪ ነው።

የማይኖሪቲስ ኮሚሺን አባል እንዲሆኑ ጥሪ የሚቀርብልቸው “የብሔረሰብ ወኪል ነን” የሚሉ አካላት የድጋፍ ፊርማ እንዲያሰባስቡ በቅርቡ የቤት ስራ እንደሚሰጣቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። በፕሮፖዛሉ መሰረት የሚሰበሰበው የድጋፍ ፊርማ ቀዳሚ ግቡ የፌዴራል መንግሥትን ጫና ውስጥ መክተት ነው ።

አናሳ የተባሉ ብሔረሰቦችን ወክለናል የሚሉ አካላት በመሰረቷቸውና በቅርቡ በሚመሰርቷቸው ፓርቲዎች ስም ምርጫ ቦርድ ‘አገር አቀፉ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ገደብ ይካሄድ’ የሚል ግፊትና ጫና እንዲፈጠር ማድረግ የሂደቱ አካል መሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

የአናሳ ብሔረሰቦች ኮሚሽን ምስረታው ዕቅድ ይሳካም አይሳካም በሁሉም አቅጣጫ የፌዴራል መንግሥቱ ላይ ውጥረትና ጫና መፍጠር የህወሃት ዓላማ ነው። ልሳነ ዐማራ ገፅ የተገኘ መረጃ

0Shares