ኢትዮጵያ በሴካፋ ውድድር እንደማትሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ

ኢትዮጵያ በመጪው ቅዳሜ ኡጋንዳ ውስጥ በሚጀመረው የምሥራቅ እና መካከለኛው አፍሪካ የእግር ኳስ ውድድር /ሴካፋ/ እንደማትሳተፍ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

ኢትዮጵያ ከኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 9 ቀን 2012 ዓ.ም በሚካሄደው ውድድር እንድትሳተፍ የምድብ ድልድል ውስጥ ብትካተትም ፌዴሬሽኑ ከውድድሩ ከሚገኘው ጥቅምና ከሚወጣበት ወጪ አንጻር መሳተፉ አስፈላጊ አለመሆኑን ገልጿል።

የፌዴሬሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ባህሩ ጥላሁን ለኢዜአ እንዳረጋገጡት ፌዴሬሽኑ ያለውን ውስን በጀት ለሴካፋ ውድድር ማዋሉ ጠቃሚ እንዳልሆነ ያምናል። አንድ ውድድር የሚለካው በተሳትፎ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ጥቅሞች ተገምግመው ነው ያሉት ዳይሬክተሩ፣ ከዚህ አንፃር ኢትዮጵያ በውድድሩ ላይ እንደማትሳተፍ አረጋግጠዋል።

yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares