ማህበሩ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ስጦታ አበረከተ
By: Date: November 18, 2019 Categories: ሁነቶች Tags:

የአዲስ አበባ ከተማ ሴቶች ማህበር ለኢ/ር ታከለ ኡማ በህጻናትና እናቶች በመደገፍ በኩል ላበረከቱት አስተዋጽኦ ስጦታ አበረከተ፡፡ ማህበሩ 7ኛውን መደበኛ ጉባኤውን አካሂዷል፡፡ በጉባኤው ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማ ተገኝተዋል፡፡

የሴቶች ማህበሩ ኢ/ር ታከለ ኡማና የከተማ አስተዳደሩ በተያዘው አመት በስፋት የተጀመረው የተማሪዎች የምገባ መርሀግብር የመሪነት ሚና በመጫወታቸው ፤እንዲሁም የተማሪዎችን የመማሪያ ቁሳቁስና ዩኒፎርም አቅርቦት ላይ የከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር በማህበሩ አድናቆት ተችሮታል፡፡

ከዘህ በተጨማሪም በክረምቱ የአረጋውያንን ቤት በማደስ ከተማ አስተዳደሩ ያከናወነው ተግባር የሚመሰገንና መቀጠልም ያለበት ነው ተበሏል፡፡ ለእነዚህና የከተማ አስተዳደሩ ሴቶችና ሀጻናትን በሚመለከት ላከናወናቸው ተግባራት ምስጋና መገለጫ የሚሆን የ”ካባ” ስጦታ ለኢ/ር ታከለ ኡማ ተበርክቶላቸዋል፡፡

ኢ/ር ታከለ ኡማ የከተማ አስተዳደሩ ለሴቶችና ህጻናት የሚሰጠው ትኩረት ቀጣይነት ያለው መሆኑን ጠቅሰው”ለሴቶች ፣ህጻናትና አረጋውያን የማትመች ከተማን መፍጠር አንፈልግም ” ብለዋል ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *