የአማራ ክልል ምክር ቤት የአራት ዳኞችን ሹመት በማፅደቅ ጉባኤውን አጠናቀቀ


የአማራ ክልል ምክር ቤት 14ኛ መደበኛ ጉባኤ በክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ለደብረብርሃን ቋሚ ምድብ ችሎት የሚሰሩ የ4 ዳኞች ሹመት በመስጠት ተጠናቀቀ።

ሹመቱ የተሰጣቸው በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በሥራ ልምዳቸውና በብቃታቸው ተለይተው የተመረጡ መሆናቸውን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ተወካይ ፕሬዚዳንት አቶ አብዬ ካሳሁን ለምክር ቤቱ አስረድተዋል።

በእዚህም የዳኝነት ሹመት የተሰጣቸው ወይዘሮ መሰረት መንግስቱ፣ አቶ ማህተመ ሰይፉ፣ አቶ ቸርነት ገብረጻዲቅና አቶ ማዕረግ ሰንደቁ ናቸው።


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares