የአግሪቴክ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ሊካሄድ ነው
By: Date: November 8, 2019 Categories: ዜና Tags:

የአግሪቴክ ኤክስፖ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ከህዳር 5 እስከ 7 ቀን 2012 ዓ.ም ሊካሄድ ነው፡፡

ኤግዚቢሽኑ በግብርና ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን የኢትዮጵያን የግብርና ኢንዱስትሪ ከቴክኖሎጂ ጋር ለማስተዋወቅ ያግዛል ተብሏል፡፡

በፋልተን ኢንዱስትሪያል ማርኬቲንግ አዘጋጅነት በሚካሄደው በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ የግብርና ማሽኖች፣ ግብዓቶች እና በዘርፉ የተገኙ አዳዲስ ፈጠራዎች ለእይታ እንደሚቀርቡ ተገልጿል፡፡

ኤግዚቢሽኑ አዳዲስ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን ለአርሶና አርብቶ አደሩ ለማስተዋወቅ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተነግሯል፡፡

በግብርና ቴክኖሎጂ ላይ የተሰማሩ 45 የአገር ውስጥና የውጭ አገር ኩባንያዎች በኤግዚቢሽኑ ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *