በጆሐንስበርግ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮያውያን ህጻናት ተለቀቁ

በጆሐንስበርግ ከተማ ደቡብ አፍሪካ በወንጀለኞች ታግተው የነበሩ ሶስት ኢትዮጵያውያን ህጻናት ተለቀው በፕሪቶሪያ ከተማ በሰላም ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቅለዋል፡፡

ህፃናቱ ከወንጀለኞች ነፃ የወጡት በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከደቡብ አፍሪካ የጸጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ከፍተኛ ጥረት እንደሆነ ተነግሯል፡፡

የህጻናቱ ወላጆችና ቤተሰቦች ልጆቻቸው ከወንጀለኞች እጅ በሰላም መለቀቃቸው እጅግ እንዳስደሰታቸው የገለጹ ሲሆን፣ ኤምባሲው እና የደቡብ አፍሪካ ፖሊስ ላደረጉት ከፍተኛ ጥረትም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙ አካላት በህግ ተጠያቂ እንዲሆኑና ተገቢውን ቅጣት እንዲያገኙም ኤምባሲው፤ ከህጻናቱ ቤተሰቦችና ከህብረተሰቡ ጋር በጥምረት ይሰራል ተብሏል፡፡

በፕሪቶሪያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ የዜጎችን መብትና ጥቅም ለማስከበር እንዲሁም በዜጎቻችን ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ወንጀለኞችን በህግ ለመፋረድ ለሚያደርገው ጥረት ህብረተሰቡ ከጎኑ እንዲቆም ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *