ቄሮ በሚል ስም ተደራጅቷል የተባለ ቡድን ተከሰሰ

ተከሳሾች እራሳቸውን ቄሮ ብለው የተደራጁ ግለሰቦች ሲሆኑ ከሳሹ ደግሞ በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ነው:: ስብሰባን ለማወክ እና ጥቃት ለመፈፀም በማቀድ የስብሰባ አዳራሽን ጥሶ በመግባትና በማስፈራራት አውከዋል ክብርን የሚነካ ስድብ ተሳድበዋል የመብት ጥሰትም አድርሰዋል ተብሎአል።

ባለፈው ዓመት በፍራንክፈርት እና በበርሊን ከተሞች በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የሚመክር የውይይት መድረክ ተዘጋጅቶ ነበር። በወቅቱ በተሰብሳቢዎች በአዘጋጆቹና በዕለቱ የክብር እንግዳ ላይ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎች ጭምር በቪድዮ በተሰራጩ መልዕክቶች ስብሰባውን ለማወክ እና ጥቃት ለመፈፀም ያቀዱ ግለሰቦች ተደራጅተው መጥተዋል።

በር ላይም ሳይፈተሹ የጥበቃ ሰራተኞችን ጥሰው የአዳራሹን በር በቡድን በሃይል በርግደው በመግባት እና በማስፈራራት አውከዋል ክብርን የሚነካ ስድብ ተሳድበዋል የመብት ጥሰትም በአዘጋጆቹ እና በተሰብሳቢዎች ላይ ፈፅመዋል በማለት የዝግጅቱ አስተባባሪዎች ለፖሊስ በማመልከታቸው የጀርመን ፖሊስ አባላት

የአዳራሹን እንቅስቃሴ በሺድዮ በመቅረፅ እና አዘጋጆቹ ሁከት ፈጣሪ ናቸው ያሏቸውን ስም እና አድራሻ በመዝገብ የአንዳንዶቹንም አሻራ በመውሰድ ማሰናበታቸውን በወቅቱ ገልፀን ነበር። ድርጊቱ በተከሰተበት ወቅትም ረብሻ እንደማይፈጥሩ የገለፁት ገብተው

በስብሰባው ቢሳተፉም በርካታ አባላቶቻችን አስቀድመው አዳራሹን ስለሞሉት ፈርተው የወሰዱት እርምጃ ነው በኦሮሞ እና ቄሮ ላይ የተዛባ አመለካከት አላቸው አባሎቻችን ከስብሰባው የተባረሩት በብሄር እና ሃይማኖት ተለይተው ነው በማለት ቅሬታ አሰምተው ነበር ፤ በተለያዩ የኦሮሞ ብሄረሰብ አደረጃጀቶች ተሰባስበው ስብሰባውን ለመታደም የመጡት ወጣቶች።

በጉዳዩ ላይ ልዩ ልዩ ማስረጃዎችን ስሰበስብ ቆይቻለው ያለው በጀርመን የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ጥበቃ ኮሚቴ በበኩሉ ራሳቸውን ቄሮ በሚል ስም አደራጅተው በጀርመን የተለያዩ ከተሞች ኢትዮጵያውያን በአዲስ አበባ ጉዳይ ለመምከር የጠሩትን ስብሰባ በኃይል ለማወክ እንዲሁም አካላዊ እና ሥነ ልቦናዊ ጥቃት

ለማድረስ ድንበር ተሻጋሪ የወንጀል ድርጊት ፈፅመዋል ባላቸው ግለሰቦች ላይ በፍራንክፈርት ከተማ ፍርድ ቤት ክስ መመስረቱን አስታወቋል። የኮሚቴው ዋና ሊቀመንበር አቶ ስዩም ኃብተማርያም በተለይ ለዶይቼ ቨለ እንዳስረዱት እነዚሁ ግለሰቦች በስብሰባው አዘጋጆች እና

በዕለቱ የክብር እንግዳ ላይ የኃይል ጥቃት እንደሚፈፅሙ በማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በሺድዮ ጭምር መልዕክቶችን ከማስተላለፋቸውም ሌላ ዘር እና ሃይማኖት ተኮር ስድቦችን በመሳደብ ተሰብሳቢዎችን በመተናኮል እና በማሸማቀቅ እንዲሁም ፎቶግራፍ እና ቪድዮ እያነሱ በማስፈራራት ከፍተኛ የመብት ጥሰት እና ሽብር ፈፅመዋል ሲሉ ከሰዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *