በቃሉ ወረዳ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ የመከላከል ሥራ ከባድ መሆኑ ተገለጸ፡፡


በደቡብሎ ዞን ቃሉ ወረዳ የተከሰተው የአንበጣ መንጋ በሰብልና እንስሳት መኖ ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑን ባልደረባችን አሊ ይመር ከቦታው የታዘበውን ገልጿል፡፡
የአካባቢው አርሶ አደሮች

ተማሪዎች፣ የልዩ ኃይል አባላትና ሌሎችም በባሕላዊ መንገድ እያደረጉ ያለው የመከላከል ጥረት ብዙም ውጤት አለማምጣቱን ነው ያመለከተው፡፡ ‹‹አሁን ደክመናል፤ በተስፋ መቁረጥ ስሜት ተውጠን የሚሆነውን ሁሉ ቁጭ ብለን እያዬን ነው›› ብለዋል አርሶ አደሮቹ፡፡

የተቀናጀና በአውሮፕላን የታገዘ የኬሚካል ርጭት አስፈላጊ መሆኑን ያመለከተው ዘጋቢያችን በሰው ጉልበትም ለመከላከል ተጨማሪ አዲስ ጉልበት እንደሚያስፈልግ አመላክቷል፡፡


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares