ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያመጣል የተባለው ወርቅ የማውጣት ሥራ በዚህ ዓመት ይጀመራል
By: Date: October 16, 2019 Categories: ኢኮኖሚ

በዓመት ከ200 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ያስገኛል ተብሎ የሚጠበቀውና የኢትዮጵያ መንግሥት ከእንግሊዙ ቱሉ ካፒ ኩባንያ ጋር በጣምራ የሚያከናውኑት የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሥራ በተያዘው በጀት ዓመት እንደሚጀመር ተገለፀ።

በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን ገንጂ ወረዳ ላለፉት 10 ዓመታት ጥናት ሲደረግበት የነበረው ፕሮጀክት የወርቅ ማዕድን የማውጣት ሥራው በዚህ ዓመት ተግባራዊ እንደሚሆን የዞኑ አስተዳዳሪ አቶ ኤልያስ ኡመታ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ አስታውቀዋል።

አስተዳዳሪው እንደገለፁት የፕሮጀክቱ 20 በመቶ ድርሻ የኢትዮጵያ መንግሥት 80 በመቶው ደግሞ የእንግሊዙ ኩባንያ ነው። ወርቅ የማውጣት ሥራው ሲጀመርም እስከ 10 ሺ ለሚደርሱ ሰዎች የሥራ ዕድል ይፈጥራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *