ከሕገ መንግሥቱ ድንጋጌ ውጭ መሬት እንደሚሸጥ የኢንስቲትዩቱ ጥናት አመለከተ


መሬት በህገ መንግስቱ ከተደነገገው ውጭ እንደሚሸጥ ከተሸጠ በኋላም ገዢዎች እንደሚነጠቁ የፍትህ አካላት መረጃ የመስጠትና የተጠያቂነት መጓደል እንደሚታይባቸው በጥናት ማረጋገጡን የፌዴራል የፍትህ የህግ ምርምርና ስልጠና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የኢንስቲትዩቱ የምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ምትኩ ማዳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት በ2011 ዓም በጀት ዓመት የመሬት ይዞታ ዋስትና ማስተላለፍ የፍትህ አካላት የመረጃ ተደራሽነትና ተጠያቂነት ላይ ጥናትና ምርምር በክልሎችና በፌዴራል ተቋማት ላይ ማድረጉን ገልጸው

 

በህገ መንግስቱ መሬት የብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች የማይሸጥ የማይለወጥ የጋራ መሆኑን ቢደነገግም፤ በተደረገው ጥናት ግን መሬት ለሽያጭ ይቀርባል ከተሸጠም በኋላ ህገ ወጥ ነው ተብሎ ከገዥው በመንጠቅ ባለቤቱ አላግባብ እንደሚጠቀምበት ይደረጋል ተብሏል።


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares