በኦሮሚያ ክልል የጦር መሳርያ አዘዋዋሪው ተቀጣ


በኢሉአባቦር ዞን ሁሩሙ ወረዳ ህገወጥ የጦር መሳርያ ሲያዘዋውር የተገኘ ግለሰብ ፍርድ ቤት ቀርቦ በእስራትና በገንዘብ ተቀጣ። የወረዳው አቃቢ ህግ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ብዙአየሁ ምትኩ እንዳሉት

ሰይድ አደም የተባለው ግለሰብ ላይ ቅጣቱ የተወሰደው የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ ሶስት 00610 አዲስ አበባ በሆነ መለስተኛ አውቶብስ ከመቱ ወደ አዲስ አበባ የጦር መሳሪያዎችን ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በመያዙ ነው።

በትላንትናው እለት በሁሩሙ ኬላ በተደረገው ፍተሻ ከበርበሬ ጋር በጆንያ ተደብቀው የተገኙት የጦር መሳሪያዎች ስምንት የተለያዩ ጠመንጃዎችና 82 የሽጉጥና የጠመንጃ ጥይቶች መሆናቸውን ገልጸው

ግለሰቡም ወዲያውኑ ለፍርድ እንዲቀርብ መደረጉን አስረድተዋል። ጉዳዩን የተመለከተው የወረዳው ፍርድ ቤትም የክስ መዝገቡን መርምሮ በሁለት አመት ከስድስት ወር እስራትና በ3ሺህ ብር እንዲቀጣ መወሰኑን ገልጸዋል።


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares