በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት የተገነባው ብርሃን የህፃናት ማዕከል ተመረቀ


በቀዳማዊት እመቤት ጽህፈት ቤት በአስራ ሁለት ሚሊዮን ብር የተገነባው ብርሃን የህፃናት ማዕከል ዛሬ ተመርቋል። በምረቃ መርሀ ግብሩ ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማና ሌሎች የመንግስት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል።

የህፃናት ማዕከሉ በ820 ካሬ ሜትር ስኩዬር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን ለዘጠና ስድስት ያህል ህፃናትና ታዳጊዎች ማሳደጊያነት እንደተዘጋጀ ተገልጿል። የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናት ማሳደጊያ ማዕከል ታህሳስ ሃያ ስምንት የእሳት ቃጠሎ ደርሶበት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ቀዳማዊት እመቤቷ ጎብኝተውት ነበር።

 


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares