መንገዱን ስቶ የተገለበጠ መኪና የስድስት ሰዎችን ሕይወትን ቀጠፈ


መንገዱን ስቶ የተገለበጠ መኪና እግራቸውን በመታጠብ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡ በአማራ ክልል ምሥራቅ ጎጃም ዞን እናርጅ እናውጋ ወረዳ ፈለገ ዛቸና ቀበሌ ዛሬ ጥዋት 4፡00 ላይ ነው አደጋው ያጋጠመው፡፡

ከባሕር ዳር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ የነበረ መለስኛ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ መስመሩን ስቶ በመገልበጡና እግራቸውን በመታጠብ ላይ የነበሩ ስድስት ሰዎች ላይ በመውደቁ የስድስቱም ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል፡፡

የምሥራቅ ጎጃም ዞን ፖሊስ መምሪያ የሕዝብ ግንኙነት አስተባባሪ ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው እንደገለጹት በመኪናው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች ግን ምንም ጉዳት አልደረሰባቸውም፡፡

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ እንደሆነና አሽከርካሪውን በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትል እያደረገ መሆኑንም ዋና ኢንስፔክተር ጎበዜ ይርሳው ተናግረዋል፡፡


yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

0Shares