ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የልብ ማዕከልን ጎበኙ


137

በማዕከሉ ህክምናቸውን በመከታተል ላይ ያሉ ልጆችንም ተዘዋውረው ተመልክተዋል፡፡ ፕሬዝዳንቷ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግም ለልጀቹ ስጦታ አበርክተዋል፡፡

ከተመሰረተ አስር አመታት ገደማ የሆነው ማዕከል እስካሁን ድረስ ከአራት ሺ በላይ ለሚሆኑ ልጆች ነጻ የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎት ሰጥቷል፡፡

ማዕከሉ የሚያደርጋቸው የስራ እንቅስቃሴዎች የሚያስደስቱ መሆናቸውን ያመለከቱት ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን ምን አይነት ታላቅ ስራ መስራት እንደምንችል ያየንበት ነው ብለዋል፡፡

ምንጭ:- የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት


Like it? Share with your friends!

137
yeahun

0 Comments

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Pin It on Pinterest