የትራንስ ኢትዮጵያ አዲስ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር በጅቡቲ ቆመው የነበሩና የኩባንያው ንብረት የሆኑ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ከትናንት በስቲያ ሰኞ ጥር 03 ቀን 2013 ዓ.ም ተረክበዋል።
ተሽከርካሪዎቹ ሕወሓት በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ላይ ጥቃት ከመፈፀሙ ጥቂት ቀናት በፊት የቀድሞ የትራንስ ኢትዮጵያ አመራሮች ከጅቡቲ ወደብ እቃዎችን ለማምጣት በሚል ወደ ጅቡቲ ወስደው እንዲቆሙ ያደረጓቸው ናቸው፡፡ በጅቡቲ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ባደረገው ጥረት አሁን ላይ ተሽከርካሪዎቹ ወደ ሀገር እንዲመለሱ ለማድረግ የቁልፍ ርክክብ መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
አዲሱ የትራንስ ኢትዮጵያ ኩባንያ ተወካይ ከጅቡቲ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስቴር የኩባንያው ንብረት የሆኑ 179 ከባድ ተሽከርካሪዎችን ቁልፎች ተረክበዋል። ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ፈቃደኛ ከሆኑት 14 አሽከርካሪዎች በስተቀር ቀሪዎቹ በጅቡቲ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያ እንደሚገኙም ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡ ሙሉ መረጃውን ከአል አይን ድረ ገጽ ያገኛሉ
Categories
More Stories
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአገር ላበረከቱት አስተዋፅኦ በውጭ በሚኖሩ የሃድያ ዞን ተወላጆች የ2020 ሞዴል መኪና ተበረከተላቸው
ቤተመንግስቱን ሊለቁ ቀናት የሚቆጥሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በለሊት በረራ ወደ ኬኒያ መላካቸው ተሰማ
ኢዜማ የክልል ልዩ ኃይል ወደ መከላከያ ወይም ፖሊስ ሊካተት ይገባል ሲል ጠየቀ