Wed. Jan 27th, 2021

Ethiopian Intercept

We Share News

ሩሲያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማክበር ቁርጠኛ አቋም እንዳላት ተረጋግጧል- ሚኒስትሮቹ

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ከሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ጋር ውይይት አድርገዋል። በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ እና ሩሲያን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት በተመለከተ መሪዎቹ ውይይት አድርገዋል።

አቶ ደመቀ መኮንን እና የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ሀገራቱ በንግድ ፣ ኢኮኖሚ ያላቸውን የሁለትዮሽ ትብብር ማስፋት በሚቻልበት ዙሪያ መክረዋል። እንዲሁም በባህል እና በሰብዓዊ ጉዳዮች ግንኙነታቸውን ለማሻሻል ምክክር አድርገዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ለሰርጌ ላቭሮቭ የፌዴራል መንግስት ህገ መንግስትን ለማስከበር በትግራይ ክልል ስለወሰደው እርምጃ ገለፃ አድርገዋል። ሩሲያ የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና ግዛታዊ አንድነት ለማክበር የማይናወጥ አቋም እንዳላት መረጋገጡትን ሚኒስትሮቹ በውይይታቸው ላይ አንስተዋል።

Subscribe To Our Newsletter

[mc4wp_form id="318"]