በመጽሐፉ ላይ ዳሰሳ የሚያቀርቡት ታዋቂው ምሁር ዳኛቸው አሰፋ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ በክብር እንግድነት ፕሮፌሰር ብርሃኑና አርቲስት ደበበ እሸቱ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡ የመድረኩ መሪ አርቲስት አዜብ ወርቁ ስትሆን፣ በመርሐ ግብሩ ላይ ተጋባዥ እንግዶች፣ የአቶ አንዳርጋቸው አድናቂዎች እና ሌሎች ተሳታፊዎች ይገኛሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የመርሐ ግብሩ አዘጋጆች ገልጸዋል፡፡
“የታፋኙ ማስታዎሻ” የተሰኘው በዶዮ አሳታሚዎች የታተመ መጽሐፍ በአራት ክፍሎች እና በ308 ገጾች ተቀንብቦ የቀረበ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን የእገታ እና የእስር ዘመናት የሚዳስስ መጽሐፍ ነው፡፡
“ለብቻዬ አንድ ክፍል ውስጥ ከታሰርኩ ወራት አለፉ፡፡ ምንም ወሬ ምንም እንቅስቃሴ የለም፡፡ አንዴ በቀን ቤቱ ይከፈታል፡፡ በሃይላንድ የሰበሰብኩትን ሽንቴን እደፋለሁ፡፡ ምግብ ይመጣል፣ ምግብ የበላሁበት ዕቃ ይሰበሰባል፡፡ ክፍሉ መልሶ በደቂቃዎች ውስጥ ይዘጋል፡፡
ክፍሉ መስኮት የለውም፡፡ በአንድ በኩል ያለው ግድግዳ ጣሪያው ጥግ ጠባብ ቀዳዳ ተበጅቶለታል፡፡ ቀዳዳው እኔ መድረስ ከማልችለበት ከፍ ያለ ቦታ ላይ የተቦረቦረ ነው፡፡ በመሆኑም ወደ ውጭ ማየት አልችልም፡፡ ጭል ጭል የምትለው የፀሐይ ብርሃን የምትገባው በዚህ ቀዳዳ ነው፡፡ መንጋቱንና መምሸቱን የማውቀው በዚህ ቀዳዳ ከማየው የብርሃን መጠን ነው፡፡በተረፈ በታሰርኩበት ክፍል ቀንና ማታ፣ ሃያ አራት ሰዓት ሙሉ የማይጠፋ የኤሌክትሪክ ብርሃን አለው፡፡ ከዚህ ብርሃን እረፍት የማገኘው መብራት ሲቋረጥ ብቻ ነው፡
መብራቱ ለእኔ አዝኖ ነው መሰለኝ በየጊዜው ይቋረጣል፡፡ ሲቋረጥ እስኪመጣ ድረስ ጨለማ ውስጥ መቀመጥ ነው፡፡ ወደ ታሰርኩበት ክፍል ነፋስ የሚገባው በዚያች ግድግዳው ላይ ባለችው ቀዳዳ ነው፡፡ ነፋሱ በቀዳዳው የምትገባውን የፀሐይ ብርሃን ተከትሎ እየገባ ይጎበኘኛል፡፡ ጨዋነት ግን ይጎድለዋል፡፡ ሲፈልገው ብርዳም ጓዙን ይዞ ይመጣል፡፡ ሲያሻው ብናኝ ተላብሶ እየመጣ የአስሜን ሕመም ሊቀሰቅስብኝ ይሞክራል፡፡
Categories
More Stories
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው
የመሬት ወረራን ጨምሮ በኮንዶሚኒየምና የቀበሌ ቤቶች ላይ ሕገወጥ ተግባር የፈጸሙ በሕግ ሊጠየቁ ነው