Wed. Jan 27th, 2021

Ethiopian Intercept

We Share News

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀይ ቦኔት (ኮፊያ) እንዴት ወደ አግዓዚ ሄደች?

“የዚህ ምስል መለያ(መለዮ) ትንሽ ውጅንብር ለፈጠረባቹህ እውነተኛ ታሪኩን በግላጭ ልገልጽ እሞክራለው(ተቃውሞ ካለም ለመቀበል ዝግጁ ነኝ) ይህ በፎቶው ላይየምንመለከተው የጠቅላይ ሚንስትሩ ነው? የኔ ምላሽ አዎ! ነው ይሄ ፎቶ የአግአዚ መለያ ነው? የኔ ምላሽ አይደለም(አርባ አራት ነጥብ)

እስከ 1987 ድረስ አራቱም ኢህአዴግን ያዋቀሩት ፓርቲዎች የራሳቸው ወታደሮች ነበራቸው፡፡ከሽግግር መንግስት ቦሀላ ሰራዊቱን በአንድ ማእከል ማዋቀር ግድ ይል ስለነበረ የተለያዩ ክፍለ ጦሮች ሲመሰረቱ በአቅምም በጥራትም ከነበሩት የተዋቀረው ደግሞ 20ኛ ቃሉ ኮማንዶ ክ/ጦር ሲሆን ከሌሎቹ በተሻለ መልኩ ሙሉ በሜካናይዝድ ክ/ጦር እና ሶስት ኮማንዶ ብርጌዶችን የያዘ መለያውም(መለዮው) ቀይ ቦኔት ነው(የአሁኑ አግአዚ የሚጠቀምበት ማለት ነው፡፡

20ኛ ቃሉ እንደተመሰረተ ማእከሉ መሀል አ.አ ውስጥ ሲሆን ኢህአዴግ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰላም አስከባሪ ሀይሎችን ሲልክ የነበረውም ከዚሁ ከ20ኛ ቃሉ ኮማንዶ ክ/ጦር ነበር ፡፡ይህንን ክ/ጦር ለየት ያደርገው የነበረው የሜካናይዝዋ የታንክ፣የመሳሪያ፣የተሽከርካሪ እና ብረት ለበስ(BRDM,ፐምፐ) ተሽከርካሪዎች ጥገና የሚያደርጉት ምልስ የቀድሞ ጦር አባላት ብቻ ነበሩ፡፡ በ1990 ኤርትራ ወረራ እንደከፈተች 20ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር ወደ ጦር ግንባር መግባትዋ ግድ ይል ነበር፡፡ ለማስታወስ ያህል በወቅቱ አንድ ዘፈን በተከታታይ በኢትዮጵያ ሬድዮም ሆነ ቴሌቪዥን ስንሰማት የነበረችው ነበር የሚለው፡፡

1991 ፆረና ልዩ ስሙ እግሪ መኸል በተባለው ግንባር የ20ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር ማጥቃት እንዲከፍት ሲገደድ የክፍለጦርዋ አዛዥ የነበረው የኦሮሞ ተወላጅ የኮሎኔል ማእረግ ያለው “ይህ የውግያ እቅድ ሊሆን የማይችል እና በውስጡም አሻጥር ያለበት የሚመስል ነው” በማለት ተቃውሞታል፡፡

.የእግሪ መኸል መሬት እንኳን አንድን ሙሉ የክ/ጦር ሜካናይዝድ ሀይል ቀርቶ አንድ መኪና እንኳን ሊያሳልፍ የማይችል ሰበርባራ መሬት እንደሆነ አየታወቀ ነው ትእዛዙ የተላለፈው(ይህን ትእዛዝ የሰጠው መለስ ዜናዊ ሲሆን እነ ስየ ተቃውመውት ነበር)

መጋቢት 5,1991 ንጋት 11 ሰአት 20ኛ ኮማንዶ ማጥቃት እንድትከፍት እንደታዘዘ ሻእቢያ ሰራዊቷን ወደ ሁዋላ መሳብ ጀመረች፡፡(ይህ የሻእቢያ ከባድ ስልት ሲሆን የህወሀት ወታደራዊ ሳይንስ እጥረትን ሚያመላክት ነበር)ሻእቢያ ሰራዊቷን እንዲያፈገፍግ ያደረገችው የኛ ጦር በጠባቡ የመግደያ መሬት እስኪገባላት ነበር፡፡ ለምሳሌ ያህል 20ኛ ክ/ጦር ከታጠቀው 53ታንኮች 42ቱን በዚህ ግንባር አሰማርቷል፣21 ዙ23 የሚባሉ ከባድ መሳሪያዎችን እና ሌሎች ብዛትያላቸው 130 እና 122 የተባሉ መድፎች የፆረናን ምድር አልብሰውት በአንድ መስመር ሲግተለተሉ ሻእቢያ ቀድማ የሞርተር ተኩሶችን ያወረደችው ቀድማ መዝግባ ባስቀመጠችው ከሁዋላ ጭራ ላይ የሜካናይዝዱ ኮንቮይ ላይ ነው፡፡

እንደ ዝናብ የሚወርዱት የሻእቢያ ቅንቡላዎች(ተተኳሾች )አንድም መሬት ላይ የሚያርፍ አልነበረም፡፡ወደ ሁዋላ እንዳያፈገፍጉ ቀድማ አንድ ታንክ ብቻ በሚያሳልፈው የሁዋላው ወሽመጥ ላይ ታንኮቹን አንድዳ መንገዱ ተዘግቷል፡፡ከዚህ ቦሀላ የተከሰተው ቀደም ሲል ከፍታውን የመግደያ መሬት ለተቆጣጠረው ሻእቢያ ቀላል ነበር፡፡የተጠመዱት 50 ካሊበሮች እና መትረየሶች ገና ከመኪና ወርደው ለመከላከል እግራቸው መሬት የረገጡትን የ20ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር አባላት እንደ ቅጠል ረገፉ፡፡ታንኮች፣መድፎች፣አየር መቃወሚያዎች እንደ ጧፍ ነደዱ፡፡በዚህ አጋጣሚ በዚህ ውግያ ላይ የተሳተፈ አንድ በቅጽል ስሙ ማንዴላ የሚባል የጢጣ(ደሴ) ልጅ ያወጋኝን እኔም በተራዬ የነገረኝ ቃል በቃል ለውጋቹ

“የጥገና ሾፕ የሆነች ኡራል ነበር የያዝኩት፡፡ውግያው አነጋግ ላይ የጀመረ ሲሆን መሸትሸት ሲል ሁሉም ነገር እንዳልሆነ ሁኖ ውግያው ተበላሽቶ የምትረግጠው መሬት አልነበረም፡፡ፍዝዝ ብየ መኪናየ ውስጥ እንደተቀመጥኩ አንድ የሻምበል ማእረግ ያደረገ ሰው ወደ እኔ በመምጣት ምንም ሳያናግረኝ ዘሎ ገቢና ውስጥ ገብቶ “ፍጠን መኪናውን አስነሳና እንሂድ” ሲለኝ ተስፋ እንደቆረጥኩ ወዴት አልኩት እንበራቂና ወደምትባለው መንደር ቢያመላክተኝም መሬቱ ሙሉ በሙሉ በአስከሬን እና የሚያነሳው ባጣ ቁስለኛ ተሞልቷል፡፡

እንቢታየን የተመለከተው የትግራይ ተወላጅ ሻምበል 45የተባለውን ረጅም ሽጉጡን መዥርጦ አናቴ ላይ እያነጣጠረ ቀጥል ንዳ ሲለኝ የግዴን ሞተር አስነሳሁ እና መኪናየን ለማዞር ሞከርኩ አይኖቼን ለመጨፈን ብሞክርም ጆሮዎቼ ግን “እባካቹህ ጨርሱን፣ውንድሞቼ ውሀ …ውሀ የሚሉትን ድምፆቸሸ ዛሬም ድረስ ያባንኑኛል፡፡ ኦራሉን አዙሬ ስነዳ አብዛኛውን ግዜ አይኔን መጨፈኑን ነበር የመረጥኩት፡፡መኪናችን ቦንብ ላይ እንደወጣ ፍንዳታ ሲያሰማ የጥይት ሳይሆን የወገናችን ጭንቅላት እንደሆነ እያወኩ ቢሆንም ምርጫ አልነበረኝም፡፡ ስንቱ መዳን የሚችሉ የወንድሞቸ አካል ላይ እንደወጣሁ አምላክ ብቻ ነው የሚያውቀው ነበር ያለኝ፡፡

የ20ኛ ቃሉ ክ/ጦር አዛዥ ከሞት የተረፈውን አሰባስቦ የሻእቢያ ማጥቃት ላይ ጸረ ማጥቃት በመፍጠር መጋቢት 7 ላይ አንዳንድ የጠላት ወረዳዎችን ቢቆጣጠርም ሌላ እስከዛሬ ከማንም ያልተተነፈሰ ታሪክ ተከሰተ፡፡ሀገራቸውን ለመታደግ በሁርሶ ማሰልጠኛ ማእከል የከተቱት ወጣቶች የ3 ወር ስልጠናቸውን ጨርሰው ለዚያ ለ20ኛ ክፍለጦር ደረሱለት(?) መድረሳቸውስ መልካም ነበር ነገር ግን ለታሪክ የሚቀመጥ ጥቁር ታሪክ ዳግም በህወሀት ኢህአዴን ተከወነ፡፡

እነዚያ ሀገራቸውን ሊታደጉ የጦር አውድማ የደረሱት ወጣቶች ወያኔ ስላላመናቸው መሳሪያ ሳይሰጣቸው ነበር ለሊት ምሽግ ውስጥ የደረሱት፡፡ይህ ጉዳይ ደግሞ ለሻእቢያ ደርሷታል(ብዛት ያለው ግን ያልታጠቀ ወጣት ሰራዊት ከምሽቱ 2ሰአት ላይ ምሽግ እንደደረሰ)አዲስ የወጣት ሀይሉ በአንድ ዝቅተኛ መሬት ላይ ነበር የሰፈረው ከሁርሶ በባቡር አዋሽ ድረስ ተጓጉዞ ቀጥሎም በተሽከርካሪ ፆረና ድረስ ስለተጓጓዘ በድካም የዛለ ነው፡፡እራቱንም ሳይሻ ባረፈበት ሁሉም እንደዛለ በተኛበት ከለሊቱ 9ሰአት ሲሆን አስደንጋጭ እና አደናጋሪ ነገሮች ተከሰተ፡፡ድንገት ሰማዩ በብርሀን ተሞላ ያ መሳሪያ ያልታጠቀ ወጣት ከሰማይ ይሁን ከምድር ምንነቱን ያላወቀው ብርሀንን ምንነት ጠይቆ ሳይረዳ እንቅልፍ ያቦዘው አይኖቹም በደንብ ሳይገለጡለት ግራና ቀኝ ካሉት የመግደያ መሬቶች ወደርሱ የሚንፈቀፈቁ መትረየሶች

በየት በኩል እንደመጣ፣ወዴት በኩል እንደሚሄድ የማያውቀው እና እንኳን ሀገሩን ራሱን የሚከላከልበት መሳሪያ ያልታጠቀው ያ ትኩስ ሀይል ላይ ሻእቢያ ግራ ቀኙን የፓውዛ ብርሀኖች በፓራሹት አየተኮሰች እንደ ሙጃ አጭዳ ከመረችው፡፡ጥቂት በህይወት ማምለጥ የቻሉት እንትጮ የደረሱ ቢሆንም “ግማሹን ከውግያ ወረዳ በመሸሽ በማለት በሞት ስትቀጣቸው የተቀሩትን አዲግራት ካለው ኢጣልያ ከሰራው የትጥቅና ስንቅ ማከማቻ ውስጥ እንደ እቃ ጠቅጥቃ በማሰር ሲሰቃዩ ነበር፡፡በወቅቱ የነበሩት የ20ኛ ኮማንዶ ክ/ጦር አባላት ስለ ሻእቢያ ሞርተሮች ኢላማ ሲናገሩ “በኪስ በኪሳችን ነበር የከተተችው” ነበር የሚሉት፡፡ብዙ ለፈለፍኩ???

እነ ጻድቃን በዚህ ውግያ ውጤት ስቅስቅ ብለው ሲያለቅሱ(የእውነት ይሁን ውሸት ባይታወቅም)የውግያውን እቅድ የተቃወመው የ20ኛ ቃሉ አዛዥ ግን ኦሮሞ በመሆኑ ኦነግ ተብሎ በጥይት ተደብድቧል፡፡ እናም 20.ቃሉ ክ/ጦር ዳግም ላትነሳ ፈረሰች፡፡ያ መለያዋ የሆነውን ቀይ ቦኔት ለገዳዩ አግአዚ ተሸጋገረ፡፡እንግዲህ ጠቅላይ ሚንስትሩ 20ኛ ቃሉ ከነበሩ ከዚህ ተአምር ማለፋቸው እውነት እንደ እድል አየዋለው፡፡ ምናልባትም የእናትየው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ ይሆን?? ለማኛውም መልካም ያሰማን፡፡ (ምንጭ የኢትዮጵያን ኢንተርሴፕት እህት ሚዲያ ቃሊቲ ፕሬስ (ተጻፈ በጉማ ሳቀታ))

Subscribe To Our Newsletter

[mc4wp_form id="318"]