አቶ ስዬ አብረሃ ጄነራል ጻድቃንና ጄነራል አበበ ተክለ ሃይማኖት ብዙ ተከታታይ የጦርነት አለሁ ባይነታቸውን በቴሌቨዥን ቀርበው ሲገልጹ ነበር፡፡ ሰው ማለት ሰው የሚሆን ነው ሰው የጠፋ ዕለት በሚለው መርህ ከሆነ ግን እንኳን እነሱ ቅርቦቻቸውም እሳቱ ዳር የሉም፡፡
ትናንት አንድ እጁን የሰጠ የትግራይ ልዩ ሃይል አባል ዝግጅታችን መከላከያን ለመዋጋት አልነበረም፡፡ ምንም ሳይነግሩን ነው እዚህ ውስጥ የከተቱን ብሎ ቃሉን ሲሰጥ ሰማሁት፡፡ እነሱ እድላቸውን በህዝብ ነፍስ እየሞከሩ ነው፡፡ በሮኬት አጻፋ ብቻችንን ከምንጠፋ አብረን ከህዝቡ ጋር እንጥፋ ባይ ናቸው፡፡
ብዙ የጦርነት ነጋሪት ጎሳሚዎች መጨረሻቸው ማረሚያ ቤት ገብቶ መቀለብ ነው፡፡ ሞት በድልም በሽንፈትም የደሃ ጽዋ ናት፡፡ እነኚህ ታጋዮች የትናንትናዎቹ አይደሉም፤ ዛሬ ለጭቆና ሳይሆን የዘረፉትን ለመብላት፤ የተመኙትን ስልጣን ላለማጣት በሚሊዮኖች ህይወት ቁማር ጨዋታ ይዘዋል፡፡
የሀገር መከላከያ ሠራዊት አጻፋን አልወደዱትም እንደ አሰቡት የሆነ አንድም ነገር የለም፤ ህዝቡን ጨርሶ በቁጣ በሚነሳ ህዝብ ዳፋ እንተርፋለን ብለው የዘረጓት ወጥመድ ተበጣጥሳለች፡፡ መከላከያ ድል ሲያደርግ የትግራይ ህዝብ እየጨፈረ ለቅሶ ለህወሃት ጁንታ ቡድን ሆኗል፡፡
እጃቸውን እንዲሰጡ የቀረበላቸውን ጥሪ እስከአሁን አልተቀበሉም፤ እነሱ ከሚታሰሩ ትግራይ ፍግም ብትል የሚመርጡ የእናት ጡት ነካሾች ናቸው፡፡ ለሚወዱት ህዝብ እልቂትን የሚመኙ ብቸኛዎቹ የህዝብ ልጆች ነን ባይ ናቸው፡፡
በኤርትራ ላይ ያደረጉት ትንኮሳና መከላከያ የእነሱ ዓይነት ጨካኝ ጠባይ እንዲያሳይ ያደረጉት ጥረት ከሽፏል፡፡ ሌላው እድላቸው ጅቡቲና ሱዳን ናቸው፡፡ አያደርጉትም ብሎ መገመቱ ቢከብድም በእነኚህ አውሬዎች ተከቦ ራሱን ወደ ጥፋት እየከተተ ያለው የትግራይ ወጣትና ህዝብ ግን አሁንም በቃ ለማለትና ጥፋቱን ለመቀነስ እድል አለው፡፡ እነሱ ያዝናሉ ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው፡፡ ደጋግመው አይተውታል፤ ደጋግሞ ጨክኖባቸዋል፡፡ (ስናፍቅሽ አዲስ በድሬ ትዩብ)
Categories
More Stories
ኢዜማ አዲስ አበባን በሚገባ የሚወክሉ ሦሥት ፕሮፌሰሮችን አሰልፏል
የአሰብን ነገር ካነሳን…ጥላሁን እምሩ (PhD)
ሱዳን እየሄደችበት ያለው መንገድ ብሄራዊ ጥቅሟን የሚጎዳ እና ዘላቂ ጥቅሟን የሚያሳጣት ነው -ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖ