Press "Enter" to skip to content

“ግብፅ 37 ቢልዮን ኲሜ ውሃ በአመት እንድትወስድ አብይ አህመድ አልሲሲን አሜሪካ ድረስ ይዞ ሄዶ አረጋግጦላቸዋል፡፡” አቶ ስዩም መስፍን

“በናይል ጉዳይ በኢህአዴግ አመራር ዘመን ታሪክ መቀየር የቻለ አኩሪ ስራ ነበረ የተሰራው፡፡ አስሩ የአባይ ተፋሰስ አገሮች ከኢትዮጵያ ጎን ተሰልፈው ግብፅን ሞግተዋል፡፡ በአባይ ጉዳይ ኢትዮጵያ ትምራን እስከማለትም ደርሰው ነበረ፡፡

አብይ አህመድ እነዚህ ከኢትዮጵያ ጥቅም ጎን ተሰልፈው ሲሰሩ የነበሩ አገሮችን ወደ ጎን በመተው እኮ ነው ወደ አሜሪካ የሄደው፡፡ እየሄድኩ ነውም አላላቸውም፡፡ ግብፅን ይዞ ነው ወደ ዋሺንግተን የሄደው፡፡ ሱዳንም በኃላ ነው ወደ አሜሪካ የተጠራችው እንጂ አብይ አልነገራቸውም፡፡

አብይ ከመጀምርያው ጀምሮ የህደሴ ግድብ ለፖለቲካ ፍጆታ የተጀመረ ነው ብሎታል፡፡ አሁን በኢትዮጵያ ህዝብ ከተቀረቀረ በኃላ ነው እየዘመረለት ያለው፡፡ ለድርድር ሲለኩ የቆዩ የግድቡ ሞያቶኞች ናቸው፤ ተው! እየተሳሳትክ ነው ያለሀው፤ የውጫሌ ሁለተኛ ስህተተ እየተሰራ ነው፤ ማቆም አለብህ ብለውታል፡፡

አብይ አህመድ ነገ ጥዋት በ treason የሚያስጠይቅ ክህደት ነው የፈፀመው፡፡ በፓርላማ ቀርቦ የ IMF እና WB እርዳታ የእናት እርዳታ ነው ብለዋል፡፡ በአሁኑ ሰአት እነዚህ ጌተቹ ምን እያሉት እንደሆነ እንመልከት፡፡ ከግብፅና ሱዳን ሳትስማማ የህዳሴ ግድብ ውሃ ሙሊት የምትጀምር ከሆነ ለማካካሻ ቃል የተገባልህ ገንዘብ አንሰጥህም ብለዋል፤ በግላጭ፡፡

በአገራችን ውስጥ የ Trump እና ዩክሬን ታሪክ እኮ ንው እየተደገመ ያለው፡፡ በ Trump እና አልሲሲ ያለው ስምምነት፣ በአድርግልኝ ላድርግልህ የተመሰረተ ነው፡፡ አብይ፣ ይህን ስራ እንዳይሰራ ከልክልልኝ፤ እኔ ደግሞ በመካከለኛው ምስራቅ ላለህ ፍለጎት አስፈፅምልሀለሁ፤ ተባብለው ነው እየሄዱ ያሉት፡፡

አብይ ይህንን ረግጦ መሄድ አይችልም፡፡ በመሃል ተንጠልጥሎ ለመሄድ የሚያስችል እድልም የለውም፡፡ የኢትዮጵያ ህዝብ ምን እያለው እንዳለም በግልፅ እየተመለከተ ነው፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፖሊሲ ደግሞ አንዴ እዛ ሄዶ ሸጦታል፡፡ በህዳሴው ግድብ ከኛ ጋር ቆመው ሲያግዙን የነበሩ አስር አገራትም አንዴ እነሱን ትቶ ስለሄደ ለብቻው ነው ወዲያ ወዲህ እያለ ያለው፡፡

ያም ሆነ ይህ እኔ ጥርጣሬ አለኝ፡፡ እኔ አብይን አላምነውም፡፡ ይህንን ግድብ ምናልባት ሊፈርስ የሚችል ከሆነ፣ አሰራሩ ፅኑ ነው፤ ወይስ አይደለም? Technical በሆኑ ጉዳዮች ብቻ ካልሆነ እያንዳንዱ ሃገር ስንት ቢልዮን ኲሜ ውሃ ይድርሳታል? ለሚለው የናይል ቤዚን ኮሚሽን ከተቋቋመ በኃላ ነው የምናየው ነው፡፡ አሁን ወደዚህ አንገባም ብለናል እኮ፡፡

ይህን በሆነበት ሁኔታ ግብፅ 37 ቢልዮን ኲሜ ውሃ በአመት እንድትወስድ አብይ አህመድ አረጋግጦላቸዋል፡፡ Trump እኮ ትንሽ ነው የጨመረው፡፡ የውሃ ሙሊትም ቢሆን ውሃ ሞምላት ጀምረናል ሊለን እኮ ይችላል፡፡ ግን የሚሞላው የውሃው መጠን ስንት እንደሆነ ማን ነው የሚለካው? በዚህ ክረምት የሚሞላው ውሃ ስንት እንደሆነ ማን ነው ለክቶ የሚነግረን፡፡

አብይ አህድ በሚሄደው የተንኮል፣ የሴራና የውርዴት መንገድ ማን ሊያምነው ይችላል? እንዴት አድርገህ ማመን ይቻላል? እኔ አላምነውም፡፡ ምክንያቱ አብይ እንዴት አድርጎ ስልጣን ላይ እንደሚቆይ ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ ግድቡ ደግሞ አንዴ ሸጦታል፡፡ በዚሁ ተግባር ከመጠየቅ አያመልጥም፡፡” ታጋይ አምባሳደር ስዩም መስፍን ከ BBC Tigrinya ጋር ከሶስት ወር በፊት ካደረገው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ

More from ፖለቲካMore posts in ፖለቲካ »

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *