Press "Enter" to skip to content

“ተረጋጉ” አርቲስት አዲስ አለም ጌታነህ ያስተላለፈችው መልእክት

“ለውድ አድናቄዎቸ እና ወዳጅ ዘመዶቸ በአጋጣሚ Internet የሌለበት ቦታ ስለነበርኩ ተገቢውን መልስ እና እኔ ጋር ያላውን እውነት ለመናገር አልቻልኩም:: አሁን ሶሻል ሚዲያ ላይ ስለሚዞረው ፎቶ እና ስለተወራው ወሬ መግለፅ እምፈልገው የጎደኛየ የቀለበት program ላይ የተነሳሁት ፎቶ ነው፡፡

የልደቴ program ላይም ጎደኞቸ በተሰባሰቡበት የልደቴን ቀን ብቻ ነው ያከበርኩት:: የታገቢኛለሽ ጥያቄም ሆነ ቀለበት ሀያት ሆቴል የተባለው ነገር ከእውነት የራቀ ነው:: “ጦር ከፈታው ወሬ የፈታው” የሚል የአባቶችን ብሂል እንዳስብ አድርጎኛል “ከላይ መነሻዬን እንድል ያስገደደኝ ይሄን ሰሞን አዲስዓለም ቀለበት አደረገች ተብሎ የተናፈሰው ወሬ እኔ ባለቤቷ ሳላውቀው ትልቅ መወያያ አጀንዳ ሆኗል፡፡

በጎ በመሆኑ ብሎኛል ምን ያህል ሰዎች ለእኔ የተሻለ ህይወትን እንድኖር እንደሚያስቡልኝ ተረድቻለሁ በዚህም አክብሮቴ ከፍ ያለ ነው:: ሁሉም ነገር በወቅቱና በስርዓቱ የማከብራቸው ቤተሰቦቼን ክብር በጠበቀ መልኩ ከራሴው አንደበት እግዚአብሔር የፈቀደ ቀን ይፋ አደርገዋለሁ፡፡

በተረፈ ቤተሰቦቼ ጎደኞቼ የምታውቁኝ በሙሉ በነገሩ ግራ እንደተጋባችሁ ገብቶኛልና እውነታውን እንድታውቁት እፈልጋለሁ የሚዲያ ሰዎችም እኔም ጋር ይሁን ጓደኞቼ ጋር በመደወል እውነታውን ለማጣራትና ለህዝብ ለማድረስ መሞከራችሁን ሳላደንቅ አላልፍም ነገር ግን እውነታው ይሄ ነውና በዚሁ አጋጣሚ እንድታደርሱልኝ እጠይቃለሁ በተረፈ ፈጣሪ በፈቀደ ቀን ምኞታችሁ እውን እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ .መቼም የህይወት አጋርን አግኝቶ ተጠቃሎ በፍቅር መኖሩ ትልቅ ክብር ነው ትዳር ከፈጣሪ ነውና

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *