Press "Enter" to skip to content

(title)

ዋለልኝ መኮንን የተወለደዉ በወሎ ሲሆን አዉሮፓ በሁለተኛዉ ዓለም ጦርነት በደቀቀችበት ዓመታት ነዉ ወደ በጠበጣት ምድር የመጣዉ። የወሎ አማራ ሳይንት ኢትዮጵያዊ ነዉ። ስምጥር ተከራካሪ መሆኑ መታወቂያዉ ነዉ። ከደርግ ስርሃት ዋዜማ ጀምሮ በኢትዮጵያ የተማሪዎች እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና ተጫዉቷል።

በተለይም ከጥላሁን ግዛዉ መገደል በኃላ ማንነቱ ገዝፏል። ዋለልኝ በጃንኦይ የንግስና የመጨረሻዎቹ ዓመታት በኮልፌ ፈጥኖ ደራሽ ታስሮ ነበር። በነገራችን ላይ እኔም የተማርኩት ኮልፌ አጠቃላይ ስለነበርኩ በእነ ዋለልኝ ዘመን ባልወለድም ቦታዉን አዉቀዋለሁ። አርቲስት ታማኝም በወያኔ ዘመን መጀመሪያ እዚያዉ ታስሮ ነበር። ገና የሃያ አራት ዓመት ወጣት እያለ ነበር እርሱ ባይፈጥረዉም ከሽኖና ቀባብቶ ያቀረበዉን የብሔርና የብሔሮች እራስን በእራስ የማስተዳደርን መብት አስፈላጊነትና የብሔሮች መገንጠልን ከፋፋይ ፁሑፍ ያቀረበዉ።

ኢትዮጵያ ሀገር ሳትሆን የብዙ ሀገሮች ጥርቅም ነች በማለትም እስካዉን እያቃጠለን ያለዉን እሳት የለኮሰዉ ወይንም እሳት መኖሩን ያሳወቀዉ እሱ ነዉ። እኔ ለዋለልኝ መኮንን ያለኝ ጥላቻና ንቀት ለመለስ ዜናዊ ካለኝ ጥላቻና ንቀት ጋር ተመሳሳይ የሚሆነዉ ሁለቱም የአንቀፅ 39 አቀንቃኞች በመሆናቸዉ ነዉ። ለምሳሌ ዋለልኝ በፁሑፉ ስለመገንጠል የሚጠቅሰዉ የሶሻሊዝም ቁንጮዉን ሌኒንን ነዉ።

የእስታሊንንም ሆነ የአልባኒያ ጎጠኛ አመለካከት ጠጥቶ ኢትዮጵያን ለመከፋፈል የሚቀባጥር ሁሉ አይመቸኝም። በነገራችን ላይ ዋለልኝ መኮንን በአስመራ አድርጎ ወደ ሮም የሚሄድ የኢትዮጵያ አዉሮፕላን ከእነማርታ ማብራቱ ጋር ለመጥለፍ ሙከራ ሂደት ዉስጥ ቢሞትም ያነሳዉም ያሟሙቀዉም የነበረዉ የብሔሮች እራስን በእራስ የማስተዳደር ጥያቄ ግን እስካሁን ኢትዮጵያችንን እየበጠበጠ አለ። (ዶ/ር መኮንን ብሩ)

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *