Press "Enter" to skip to content

ማንን እንመን?

የኦነጉ መሪ አቶ ዳዎኢድ ኢብሳ ተገምግመው የስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ ሽሯቸዋል፤ አዲስ ሊቀመንበር ተመርጧል ተብሏል። ፖሊስ ደግሞ ጉዳት እንዳይደርስባቸው ጥበቃ እያደረኩ ነው በሚል አቶ ዳዎድ እየጠበቀ ነውም ተብሏል።

በሌላ በኩል የኦነግ አመራሮች አቶ ዳዎድ ብዙ መንቀሳቀስ ስለማይችሉ (ያው የቁም እስረኛ ስለሆኑ)፣ ስራችንን መስራት ስላለብን ነው ሌላ አመራር የመረጥነው ይላሉ። በቀጥታ አልተናገሩትም እንጂ መሪያችን ዳዎድ ኢብሳ ታስሯል እያሉን ነው።

አቶ ዳዎድ ኢብሳም ሆነ ሌሎች የኦነግ አመራሮች ሰላማዊ ትግል ነው የምናደርገው ብለው በተዘዋዋሪ መንገድ የትጥቅ ትግሉን የሚመሩ አይደሉም የሚለውን ለማመን ይከብደኛል። በመሆኑም ኦነግ ላይ እርምጃ መወሰድኑን አጥብቄ እደግፋለሁ። በፊት ነው መወሰድ የነበረበት። ወለጋ አውድማ የሆነችው በኦነግ ምክንያት ነው።

በነገራችን ላይ ኦነግ ምርጫ እስኪደረግ ድረስ ትጥቁን እንደማይፈታ ከአቶ ለማ መገርሳ ጋር ተደራድሮ ነው ወደ አገር ቤት የገባው። ስለዚህ አቶ ለማ መገርሳ ለኦነጎች ፣ “እስከ ምርጫው ትጥቃችሁን አትፈቱም” የሚል ስምምነት ለምን እንዳደረገ መጠየቅ አለበት !!!!! በኦነጎችና በኦነግ ስም ለተፈጠሩት እልቂቶች በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠያቄ አቶ ለማ መገርሳ ነውና።

ይሄን ብዬ በመጨረሻ አንድ ነገር ልበል። ጃዋር ታሰረ፣ በቀለ ገርባ ታሰረ፣ አቶ ለማ መገርሳ ወደ ጎን ተገፋ፣ ዳዎድ ኢብሳ የቁም እስር ታሰረ ..…እንደዚያም ሆኖ በአንጻራዊነት መረጋጋት አለ። ያም የሆነበት ምክንያቱ አብዛኛው ዝም ብሎ ግን ውስጡ ሲድብን የነበረው የኦሮሞ ማህበረሰብ ዞር በሉ ከዚህ ስላላቸው ነው። በተለይም በነዚህ ሰዎች ምክንያት የተፈጠረው የዘር ማጥፋት እልቂትና ሰቆቃ ብዙ የኦሮሞ ልጆችን አንገት አስደፍቷል። እነበቀለ ገርባ፣ እነ ጃዋር፣ ኦነጎች ሲያይ የሚያየው በኦሮሞ ስም የተፈጸሙ ሰቆቃዎችን ነው። አንድ ግማሽ አማራ፣ ግማሽ ኦሮሞ የነበረ ሰው ኦሮሞ ነኝ ነበር የሚለው። አማራ ነኝ ማለት ሲጀምር ሳይ እነዚህ ሰዎች ምንም ያህል የኦሮሞን ብራንድ እንደጎዱት አንዱ አመላካች ነው።

ከዚህም የተነሳ ሕዝቡ በውስጡ የተሰገሰጉ፣ በስሙእ የሚነገዱ፣ ስሙን የሚያጠፉ ጽንፈኞችን ዝም ብሎ መታገስ ሳይሆን መንጥሮ ለማውጥ እንደውም የበለጠ ተዘጋጅቷል። በተለይም የሸዋ ኦሮሞዎች መነሳትና መነቃነቅ በጣም አስደሳች ብቻ ሳይሆን ለአገር ትልቅ ተስፋን የሚሰንቅ ነው። (ግርማ ካሳ)

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *