SHARE

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት እንዳስታወቀው እስካሁን በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪዎች የደም ናሙና እየተወሰደ ሲመረመር የነበረው በአንድ ቦታ ብቻ ነበር።

አሁን ላይ የምርመራ ቁሳቁሶች በመገኘታቸው እና የቫይረሱ ስርጭት እንደሚሰፋ በማመን ሁለት የመመርመሪያ ቦታዎች መለየታቸውን ተገልጿል።

የኢንስቲቲዩት ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ዛሬ ረፋድ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደገለጹት በአሁኑ ወቅት ቢሾፍቱ አካባቢ የሚገኝ ናዲክ የተባለ የግብርና ምርምር ተቋምና አርማዎር ሃንሰን የምርምር ኢንስቲቲዩት ወደ ስራ ለመግባት ዝግጁ ሆነዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በደም ውስጥ የሚኖርን የኤች አይቪ ቫይረስ መጠን ለማወቅ የሚያገለግለው መሳሪያ ኮቪድ-19 ቫይረስን የመመርመር አቅም አለው ብለዋል።

መሳሪያው በሁሉም ክልሎች በሚገኙ 19 ተቋማት ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ዳይሬክተሩ መሳሪያዎች ለኮሮናቫይረስ መመርመሪያ የራሳቸው የሆነ ኪት ስለሚያስፈልጋቸው ከአምራች ካምፓኒዎቹ ተገዝቶ እንዲቀርብ ግዥ መቅረቡንም ተናግረዋል።

በመሆኑም ከውጭ ለጋሽ ደርጅቶች የተገኙ የመመርመሪያ መሳሪያዎችን ጨምሮ በአገር ውስጥ የሚገኙት በሙሉ ዝግጁ ሲሆኑ ምርመራው እንደሚጀመር ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። ምንጭ፦ ኤፍ.ኤም አዲስ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here