SHARE

በጎንደር ከተማ አስተዳደር አዘዞ ክፍለ ከተማ 873 ሺህ 900 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላር መያዙን ፖሊስ አስታወቀ።።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር 5ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ቻላቸው የኔነህ ሀሰተኛ ዶላሩ ከህብረተሰቡ በመጣ መያዙን ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ መሠረት ከኢፌዴሪ ጉምሩክ ባለስልጣን የጎንደር ከተማ ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ እና ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል ጠቅላይ መምሪያ መረጃ ክፍል ጋር በተካሄደ ዘመቻ ሐሰተኛ ገንዘቡ መያዙን ገልፀዋል።

አንድ ግለሰብ ከእነግብረ አበሮቹ በጉዳዩ ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ዋና ኢንስፔክተሩ አስታውቀዋል፡፡

ዋና ተጠርጣሪው በተለያዩ አካባቢዎች በተለያዩ ስሞች የሚጠራ እና በሐሰተኛ መታወቂያዎች የሚንቀሳቀስ መሆኑንም ኃላፊው አብራርተዋል።

873 ሺህ 900 ሐሰተኛ የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ ዘጠኝ ኪሎ ግራም የሚመዝን ነሐስ፣ ጌጣጌጦች፣ ማዕድናት፣ የቤተ ክርስቲያን ቅርሶች የሚመስሉ ሐሰተኛ ቁሶች፣ የሐሰተኛ ዶላር ኖቶች ማባዣ ማሽን እና ሌሎች ዕቃዎች ጋር ነው ተርጣሪዎቹ መያዛቸውን አብመድ ዘግቧል።

ምንጭ፡ ኤፍ.ቢ.ሲ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here