Press "Enter" to skip to content

የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያዎችን ለማምረት በግብአትነት የሚውልን አልኮል በብዛት ለማምረት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የሚያስችሉ የንፅህና መጠበቂያዎችን ለማምረት በግብአትነት የሚውልን አልኮል በብዛት ለማምረት እየሰራሁ ነው አለ፡፡

በአሁኑ ወቅትም የንፅህና መጠበቂያ ቁሶችን ለማዘጋጀት ግብአት ሆኖ የሚያገለግለው አልኮል በፊንጫና በመተሃራ ስኳር ፋብሪካዎች 3 ሚሊየን ሊትር መኖሩን ተናግሯል፡፡

ፋብሪካዎች በቀን 100 ሺህ ሊትር ቴክኒካል አልኮል የማምረት አቅም እንዳላቸው ኮርፖሬሽኑ ለሸገር ተናግሯል፡፡

የምርት መጠኑን እያንዳንዱ ፋብሪካ በቀን እስከ 150 ሺህ ሊትር በማምረት ከዚህ ቀደም አልኮሉን ያቀርብላቸው ከነበሩ ፋብሪካዎች በተጨማሪ ለተጨማሪ 6 ተቋማት ለማቅረብ እየሰራም ነው ተብሏል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን የሚያመርተው ቴክኒካል አልኮል ከ96 በመቶ በላይ የአልኮል ይዘት አለው የተባለ ሲሆን ለሳኒታይዘር፣ ለደረቅና ፈሳሽ ሳሙናና ለዲቶል (የመፀዳጃ ቤት ማፅጃ) መሳሪያ በግብአትነት ያገለግላል ተብሏል፡፡

Be First to Comment

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *