በለንደን አንድ ዩኒቨርስቲ ውስጥ ተመራማሪ የሆነው ፕሮፌሰር ኔይሊ ፈርጉሰን ከቀናት በፊት እንግሊዝ አስቸኳይ እርምጃ መውሰድ ካልቻለች እስከ 260 ሺህ ዜጎች በኮረና ቫይረስ ሊሞቱ ይችላሉ ሲል ያስጠነቀቀ ሲሆን ዛሬ በወጣ መረጃ ግለሰቡ ራሱ በቫይረሱ ሳይጠቃ እንዳልቀረ ተዘግቧል።
ፕሮፌሰሩ በትዊተር ገጹ ላይ ዛሬ ማለዳ ላይ እንደ ገለጸው የበሽታው ምልክቶች ስለታዩበት ራሱን ከሰዎች አግልሎ ለመቀመጥ መወሰኑን ገልጿል።
Sigh. Developed a slight dry but persistent cough yesterday and self isolated even though I felt fine. Then developed high fever at 4am today. There is a lot of COVID-19 in Westminster.
— neil_ferguson (@neil_ferguson) March 18, 2020
ቫይረሱ እንግሊዝ ውስጥ ከገባ ጀምሮ ቀንና ለሊት ሲሰራ እንደነበር የገለጸው ዴይሊ ሜይል መንግስት የፕሮፌሰሩን ምክር ተቀብሎ አስፈላጊውን ሁሉ ማድረግ አለበት ብሏል።
በአሁን ወቅት 1950 እንግሊዛውያን በቫይረሱ መጠቃታቸውንና 71 ደግሞ መሞታቸው ተዘግቧል።
Categories
More Stories
መቀሌ በድምፅ አልባ መሣሪያዎች የተደራጁ ዘራፊ ቡድኖች በየመንደሩ ዝርፊያ እየፈጸሙ ይገኛሉ
ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለአገር ላበረከቱት አስተዋፅኦ በውጭ በሚኖሩ የሃድያ ዞን ተወላጆች የ2020 ሞዴል መኪና ተበረከተላቸው
ቤተመንግስቱን ሊለቁ ቀናት የሚቆጥሩት የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የአፍሪካ ጥገኝነት ጠያቂዎችን በለሊት በረራ ወደ ኬኒያ መላካቸው ተሰማ