SHARE

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም ጋር ተወያዩ። ውይይታቸው ጄኔቫ በሚገኘው የዓለም ጤና ድርጅት ፅህፈት ቤት የተደረገ ነው።

በውይይታቸውም በሁሉን አቀፍ የጤና ሽፋን በቅድመ ጤና አጠባበቅ በተመጣጠነ ምግብ በህክምና መሳሪያዎች እና ቁሳቁስ አቅርቦት እንዲሁም በአቅም ግንባታ ዙሪያ መክረዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የዓለም ጤና ድርጅት በኢትዮጵያ የጤናው ዘርፍ ልማት ለሚጫወተው አጋዥ ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል። የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም በበኩላቸው

ዓለም ጤና ድርጅት ከኢትዮጵያ ጋር ያለውን አጋርነት እንደሚያጠናክር ተናግረዋል። በውይይቱ በተነሱ ነጥቦች ዙሪያም ድርጅቱ ድጋፉን እንደሚያደርግ ማረጋገጣቸውን ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here