ኢህአዴግ ከግንባርነቱ ወጥቶ ወደ አንድ ፖርቲ ለመዋሃድ የሚያደርገው እንቅስቃሴ የሁሉንም ፖርቲዎች ፍጹም ፈቃደኝነት እና ይሁንታ ማግኘት ያለበት በመሆኑ አፈጻጸሙ ብዙ የግንባሩን መሰረቶች የሚያናጋ እና አስቸጋሪም ሊሆን እንደሚችል ተገለጸ።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፌዴራሊዝም ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰሩ ዶክተር ጌታቸው አሰፋ አንዱ ፓርቲ ካልተስማማ የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ውህደቱን አይፈቅድም ብለዋል።
ውህደት ሲፈጸም የአባላቱ ፍላጎት የአጋር ፓርቲዎችን ሁኔታ እንዲሁም የግንባሩን የጠቅላላ ጉባኤም ውሳኔ የሚሻ በመሆኑ የተራዘመ ጊዜ የሚፈጅ ጉዳይ መሆኑንም አብራርተዋል።
በግንባሩ ስር ያሉት ፓርቲዎች ስምምነት ፈጥረው አንድ ፓርቲ መመስረት ከቻሉ ግን የሃገሪቱን የፖለቲካ ድባብ የሚቀይር እርምጃ እንደሚሆን ጥሩ ጥቅምም የሚያመጣ መሆኑን አስረድተዋል።
Categories
More Stories
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው