በግብፅ ከጁምዓ ፀሎት በኋላ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰለፍ እየተካሄደ ነው፡፡ ይህንንም ተከትሎም ዋና ከተማዋ ካይሮን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
ከዕለተ አርብ ፀሎት በኋሏ ዋራቅ በሚባል አካባቢ ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ ከስልጣን እንዲለቁ የሚጠይቅ መልዕክት እያሳሙ መሆኑን አልጀዚራ ዘግቧል፡፡ ተቃዋሚዎቹ በሀገሪቱ ያለው የኑሮ መመሰቃቀል እና የሙስና መስፋፋት እንዲቆም መጠየቃቸው ተሰምቷል፡
የጁምዓ ተቃውሞ በደቡብ ግብፅ በምትገኘው ሉክሰር እና በቁስ አካባቢዎች መቀስቀሱም ተጠቁሟል፡፡ በዋና ከተማዋ ካይሮ ደግሞ የ2011 የተቃውሞ እምብርት የነበረውን የታሂር አደባባይ መግቢያ የፀጥታ አካላት እንደዘጉት ተነግሯል፡፡
ፕሬዚዳንት አል ሲ ሲ በአስተዳደራቸው ላይ የተነሳው ተቃውሞ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለፅ ለተቃውሞ ምንም ምክንያት የለም ያሉ ሲሆን የፀጥታ አካላት በዋና ከተማዋ የፀጥታ ቁጥጥሩን እንዲያጠናከሩ ማዘዛቸው የሚታወስ ነው፡፡
Categories
More Stories
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው