የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛዋ ወሮ እፀገነት አንተነህ ወይም ሊሊ መስከረም 6 ቀን 2012 ዓም በግምት ከጠዋቱ 12፡30 ሰዓት በአቃቂ ቃሊት ክፍለ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቷ ወደ ስራ ለመሄድ ትራንስፖርት በመጠበቅ ላይ እንዳለች ሦስቱ ተጠርጣሪዎች
ወንጀል ለመፈፀም አቅደው የትራንስፖረት አገልግሎት የሚሰጡ በማስመሰል ሟችን በሰሌዳ ቁጥር ኮድ 1-34039 ኦሮ ባጃጅ በሆነ ተሽከርካሪ ከሳፈሯት በኋላ አንቀው በመግደል የሟቿን አስክሬን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ቦታው ሰላም ፍሬ ጤና ጣቢያ አካባቢ መንገድ ላይ ጥለዋት ይሰወራሉ፡፡
ወንጀሉን የፈፀሙ ግለሰቦች አለመታወቁ የፖሊስን ስራ እጅግ አስቸጋሪ ቢያደርገውም የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀሉ ከተፈፀመ ጀምሮ ቀንና ሌሊት ባደረገው ከፍተኛ ክትትል ሦስቱን ወንጀል ፈፃሚዎችን ወንጀሉን በፈፀሙ በዘጠነኛው ቀን መስከረም 15 ቀን 2012 ዓም በቁጥጥር ስር ማዋል ችሏል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በርካታ የአካባቢው ሰዎችና የሟች ቤተሰቦች በተገኙበት መስከረም 16 ቀን 2012 ዓም ወንጀሉን እንዴት እንደፈፀሙት መርተው አሳይተዋል፡፡ ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም ፒያሳ አካባቢ በአንድ ግለሰብ ላይ የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ግለሰቦችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መያዙ የሚታወስ ነው፡፡
ህብረተሰቡ ወንጀለኞችን አጋልጦ በመስጠት እና ምስክር በመሆን እያደረገ ያለውን ተሳትፎ አድንቆ ይህንኑን ትብብር አጠናክሮ እንዲቀጥል የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጥሪውን አቅርቧል፡፡ የሟች እፀገነት አሟሟት በልዩ ልዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች መነጋገሪያ ሆኖ መሰንበቱ የሚታወስ ነው፡፡
Categories
More Stories
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው