የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ በ86 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡ ዣክ ሺራክ ዛሬ ጠዋት ቤተሰቦቻቸው በተሰበሰቡበት ህይወታቸው ማለፉን የመገናኛ ብዙሃን እየዘገቡ ይገኛል፡፡
የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዚዳንት ዣክ ሺራክ ለሁለት የምርጫ ጊዚያት ከአውሮፓዊያኑ አስራ ዘጠኝ ዘጠና ስምንት እስከ ሁለት ሺህ ሰባት ሀገራቸውን በፕሬዚዳንትነት አገልግለዋል፡፡ ፈረንሳይ የዩሮ መገበያያ እንድትጠቀም ማድረጋቸውንም ዘገባው አስታውሷል፡፡
ዣክ ሺራክ ከስልጣን ከወረዱ በኋላ ግን ስማቸው ከሙስና ጋር በተያያዘ ይነሳ እንደነበር ይነገራል፡፡ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ለረጅም ጊዜ በስልጣን በመቆየት ሁለተኛው ሰው እንደነበሩም ነው የተገለጸው፡፡ ከስለጣን ከወረዱ በኋላ የህልፈታቸው ዜና እስከተሰማበት ጊዜ ድርስም ቀን ከቀን የጤና ሁኔታቸው አሳሳቢ እየሆነ መጥቶ እንደነበር ነው ዘገባው የሚያስረዳው፡፡
Categories
More Stories
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው