በመላው ሀገሪቱ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ዘንድ የሚከበረው የደመራ በአል በአንድነትና በፍቅር ሊከበር ይገባል አሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንና አማኒያን ዘንድ በነገው ዕለት የደመራ በዓል ይከበራል፤ ከነገ በስቲያ እንዲሁ የመስቀል በዓል ሃይማኖታዊም ባሃላዊም ይዘቱን ጠብቆ ይከበራል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ፓትርያርኩ በመልዕክታቸው ለብዙ ዘመናት ተቀብሮ የነበረው ቅዱስ መስቀል በንግሥት ዕሌኒ አማካይነት ተቀፍሮ መውጣቱንና በመስቀሉ ያገኘነውን ሰላም፣ ዕርቅና ፍቅር እያሰብን የምናከብረው በዓል ነው ብለዋል።
መስቀል የድህነት በዓል ነው፣ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም የመስቀልና የደመራ በዓልን ስናከብር በክርስቶስ ደም የተከበረና የተቀደሰውን መስቀልን እያሰብን መሆን አለበት ብለዋል።
ህዝበ ክርስቲያኑ መስቀል የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት መታሰቢያ መሆኑን ከግምት በማስገባት የደመራውንም ሆነ የመስቀል በዓልን በሰላም በፍቅርና በአንድነት ባጠናከረ፣ መጠላላትን በናቀ መልኩ እንዲያከብሩም ፓትርያርኩ ጥሪ አቅርበዋል። አያይዘውም በበዓሉ በርካታ የውጭ እንግዶች የሚገኙ በመሆኑ ለዓለም የሰላም ምሳሌነታችንን በአደባባይ ልንመስክር ይገባናል ብለዋል።
ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር ቆይታ ያደረጉት የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ ረዳት ጳጳስ ብጹዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ በበኩላቸው በዓሉ ላይ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮች ውጪ እንደሚታደሙበት አንስተዋል። የደመራና የመስቀል በዓል ቤተክርስቲያኒቱ ለዓለም ያበረከተችው መንፈሳዊ ቅርስ እንደመሆኑ ሰላምንና አንድነትን በሚሰብክ መልኩ እንዲከበሩ ጠይቀዋል።
Categories
More Stories
ኢዜማ የቀድሞው የአዲስ አበባ ም/ከንቲባ ታከለ ኡማ በህግ ሊጠየቁ ይገባል አለ
በቢጫ ለባሾቹ ምክንያት የእነ ጃዋር ችሎት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጠበት
ሱዳናዊ ባለሀብት በአባይ ወንዝ ላይ 18 ኪሎ ሜትር ቦይ በመስራት 170 ሺህ ሄክታር መሬት በመስኖ ሊያለሙ ነው